Print PDF
User Rating: / 1
PoorBest 

በምርታማነታቸው በምርምር የተለዩ የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ-አደሩ በማስተዋወቅ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል የተሻለ ምርት የሚሰጥ “አዳማ ሬድ” የተባለ የቀይ የሽንኩርት ዝርያን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኪንፋዝ በገላ ወረዳ አድርቀይና ቀበሌ የመስኖ አዉታር ተጠቃሚ ለሆኑ አርሶ-አደሮች በማቅረብ እና ሙያዊ እገዛ በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሰራ ይገኛል፡፡ የስራውን እንቅስቃሴ ተመልክቶ ተሞክሮውን የበለጠ ለማስፋትም በቀበሌው የመስክ ቀን ተካሂዷል፡፡ በመስክ ቀኑ የእድሉ ተጠቃሚ የሆኑ አርሶ አደሮች በምርምር ማዕከሉ የቀረበላቸውን የሽንኩርት ዘር በመጠቀም በ2012 ዓ/ም የተሻለ ተጠቃሚ እንደነበሩ ገልፀው በዚህ ዓመት ግን ባለው የገበያ ሁኔታ ተጠቃሚ እንዳልሆኑ ገልጸዋል፡፡ የገበያ ትስስር ስላልተፈጠረልን በድካማችን ልክ ተጠቃሚ አልሆንም ያሉት አርሶ አደሮቹ የምርምር ማዕከሉን በማመስገን ሌሎች የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችም እንዲቀርቡላቸው ጠይቀዋል፡፡

በጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል የአፈር ምርምር ተመራማሪ አቶ አትክልት አበራ ማዕከሉ በህዝቡ ጥያቄና ፍላጎት መሰረት ለአካባቢዉ ስነ-ምህዳር ተስማሚ የሆኑ የሰብል አይነቶችን እየለየ እንደሚያስተዋውቅ ገልጸው አካባቢዉ ዝናብ አጠር በመሆኑ የአርሶ-አደሩን የምግብ ዋስትና የሚያረጋግጡ ውጤታማ የሰብል ዝርያዎችን በቀጣይ እንደሚያቀርብ ተናግረዋል፡፡ አርሶ-አደሩም በምርምር ማዕከሉ ለትዉዉቅ የሚቀርቡለትን ዝርያዎች በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ተመራማሪው አስገንዝበዋል፡፡ ከዚህ በፊት ከቀይ ሽንኩርት በተጨማሪ ምርምር ማዕከሉ የቲማቲም እና የሀብሃብ ዝርያዎችን አቅርቦ እንደነበር ያስታወሱት አቶ አትክልት ነገር ግን ዝርያዎቹን ተቀብሎ ወደ ስራ የገባው አርሶ አደር ቁጥር ትንሽ ነው ብለዋል፡፡ ይህ መስተካከል እንዳለበት የጠቆሙት ተመራማሪው ምርምር ማዕከሉ መነሻ ዘር እንደሚያቀርብ ገልጸው አሁንም ለ5 ሄክታር የሚሆን ምርታማ የሆነ የጤፍ ዘር እናስረክባለን ብለዋል፡፡ በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአፈርና ዉሃ ጥበቃ ተመራማሪ ዶ/ር ሀይሉ ክንዴ በበኩላቸው አርሶ አደሩ የቴክኖሎጅ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚደረገው ክትትልና ድጋፍ ጅምሩ ጥሩ መሆኑን ገልጸው አርሶ አደሩ ላይ የሚታየው የማሳ አያያዝ ክፍተት መስተካከል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ አርሶ-አደሩ የሚፈልገውን የምርት መጠን ለማግኘት ማሳውን በወቅቱ ማረምና መንከባከብ እዳለበት በማሳሰብ በጥያቄአችሁ መሰረት የተሻሻሉ ዝርያዎች ወደ አርሶ አደሩ እንዲደርሱ ኢንስቲትዩቱ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

t12t534tr35te53532

 

 

Last Updated ( Thursday, 24 June 2021 13:39 )  
You are here: Home News News አዳማ ሬድ