Frontpage Slideshow | Copyright © 2006-2010 JoomlaWorks, a business unit of Nuevvo Webware Ltd.

 
Print PDF
User Rating: / 2
PoorBest 

The 1st Call of Africa-UniNet will be opened from 1 AUG – 30 SEP 2020

Last Updated ( Tuesday, 04 August 2020 06:56 )
 
Print PDF
User Rating: / 5
PoorBest 

በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል ከኖርዊያን ደን ልማት ማህበር ጋር በመቀናጀት በሊቦከምከም ወረዳ ጣራገዳም ቀበሌ የሀብሀብ ፍራፍሬ ቅድመ-ማስፋት ስራዎች በመስክ አስጎበኘ

*********************************************************************************

ዶ/ር አሰፋ ደረበ የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት ምርምር ማዕከሉ የሀብሀብ ፍራፍሬን ወደ ክልሉ በማምጣት የማላመድ እና የማስተዋወቅ ስራውን ባለፉት 5 ዓመታት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል፡፡ በተለይም በሜጫ እና ደራ ወረዳዎች ሰፊ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የተናገሩት ዳይሬክተሩ በዚህ ዓመት ከኖርዊያን ደን ልማት ማህበር በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በሁለት ወረዳዎች በእብናት እና ሊቦከምከም ወረዳዎች የማስፋት ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡ ምርምር ማዕከሉ በደራና ቆጋ ወረዳዎች የማስፋት ስራዎችን በመስራቱ አርሶአደሩ የበለጠ ተጠቃሚ መሆን ገልፀዋል፡፡ ለከተምች በተለይም ለባህር ዳር እና ሜጫ ነጋዴዎች የሀብሀብ ፍራፍሬ የአቅርቦት ችግር የፈታ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ምርምር ማዕከሉ የምርምር ስራውን በአንድ አርሶአደር የጀምረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከ20-25 የሚሆኑ አርሶአደሮች ላይ መድረስ እንደተቻለ ገልፀዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም ተጠቃሚ አርሶአደሮችም ወደ ባለሀብትነት እየተቀየሩ ያለበት ደረጃ መድረስ መቻላቸውን ጠቅሰው ይህንንም የበለጠ ለማጠናከር ቴክኖሎጂዎች ሊደረሱባቸው በሚችሉ ወረዳዎች እና የአየር ንብረት ምቹ በሆነባቸው አካባቢዎች ሁሉ ለማድረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አርሶአደሩ ወደ ምርት ከመግባቱ በፊት ሙሉ የአመራረትና የአጠቃቀም መመሪያ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ የጠቀሱት ዳይሬክተሩ በሁለት መንገድ አምርቶ እንዲጠቀም ሲሆን በዋናነት የህፃናት መቀንጨር ችግርን ለመቀነስ ሲባል መጀመሪያ አምርተው ቤተሰቦቻቸውን እንዲመግቡ በተለይም ለትምህርት ያልደረሱ ህፃናት እና ተማሪዎች እየተመገቡ እንዲያድጉ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን ገልፀዋል፡፡ አርሶአደሩ በተለምዶ በሌሎች ሰብሎች እንደሚታየው ዋጋ የሚያወጣለት ከሆነ ወደ ገቢያ በመውሰድ የመሸጥ ልምድ ነው ያለው፡፡ ይህን ደግሞ ዘገምተኛ ቢሆንም በሂደት እያመረተ ህፃናትንና ተማሪዎችን እንዲመገቡ የማድረግ ስራ መሰራት አለበት ብለዋል፡፡ ዳይሬክተሩ በመጨረሻም የገቢያ ችግርን ለመፍታት የሀብሀብ ሰብል ለክልሉ አዲስ እንደመሆኑ መጠን ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ አርሶአደሩ ያመረተውን በሙሉ በመረከብ ለክልሉ ህዝብ የማስተዋወቅ ስራ መሰራቱን እንዲሁም አምራች አርሶአደሮችን ከማህበራት፣ ከነጋዴዎች ጋር ሰብሉ ከተመረተበት ቦታ ድረስ ወስዶ በማሳየት በርካታ የማስተዋወቅ እና የገበያ ትስስር ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡

የሊቦከምከም ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ ወንድአጥር ዘውዱ በበኩላቸው የሊቦከምከም ወረዳ የመስኖ አቅሙ ከፍተኛ የሆነ እና በአትክልትና ፍራፍሬ ሰብል የታወቀ ወረዳ መሆኑን ጠቅሰው አሁን ባለው ሁኔታ ከ6ዐዐዐ ሄክታር መሬት በላይ የመስኖ መሬት መኖሩን ገልፀዋል፡፡ በጣራ ገዳም ቀበሌ በባህላዊና ዘመናዊ መስኖ አውታር ስራዎች በስፍት እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰው በቀበሌው በስፍት እየተመረቱ የሚገኙት እንደ ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ጥቅል ጎመን፣ ድንች ልማት በከፍተኛ ሁኔታ ይመረታሉ ብለዋል፡፡ የሀብሀብ ፍራፍሬ ለቀበሌው አዲስ መሆኑን ገልፀው እንደ ወረዳው በሁለትና ሶስት በሚሆኑ ቀበሌዎች ከዚህ በፊት በመሞከር ይህን ለማስፍት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ ም/ኃላፊው አክለውም በጣራገዳም ቀበሌ ለአውራ መንገድ /አስፖልት /ቅርብ በመሆኑ የገቢያ ችግር ያጋጥማል የሚል ስጋት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡ ይህን ተሞክሮ በመያዝ በይበልጥ ማስፋት፣ በሌሎች አርሶአደሮች ማስጐብኘት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው በወቅቱ የተከሰተው የኮቪድ 19 ስርጭት መከሰቱ በርካታ የልማት ስራዎች እንዳንሰራ እንቅፋት ቢሆንም በኘሮግራም በመመራት አንስተኛ አርሶአደሮች ባሉበት የገበሬ በዓል በማዘጋጀት አርሶአደሮች ትምህርት እንዲወስዱ የተደረገበት ሁኔታ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ የአርሶአደሩ ፍላጐት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሊሄድ ስለሚችል በፍላጎቱ ልክ የዘር አቅርቦቱም ሊጨምር ስለሚችል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጂት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል ኃላፊው፡፡

አርሶአደር ዬሐንስ መንግስቴ የጣራገዳም ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ በምርምር ማዕከሉ የተሰጣቸውን የሀብሃብ ፍራፍሬ እያለሙ መሆናቸውን ገልጸው የሀብሀብ ሰብል ከፍተኛ የሆነ የጤና ጥቅም እንዳለው በተለይ በሽታ ከመከላከል እንደ ካንሰር፣ ኮሌስትሮ፣ የስኳር እና ሌሎች በሽታዎችን ለመከላከል ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የገበያ ምንጭ እንደሚያስገኝ ስልጠና የተሰጣቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከስልጠናው በኃላ የዘር አቅርቦት ከምርምር ማግኘታቸውን ጠቅሰው 4ዐ በ 45 ካሬ በሆነች መሬት እያመረቱ መሆኑን ገልፅዋል፡፡ ሰብሉ በትንሽ መሬት ላይ ከፍተኛ የሆነ ምርት ሊሰጥ እንደሚችል የገለፁት አርሶአደሩ በቀጣይ የበለጠ ተጠቃሚ ያደርገናል የሚል ተስፋ እንዳላቸው እና በስፋትም ለማምረት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ አርሶአደሩ የገበያ ትስስር ችግር እንደይገጠመን የሚመለከታቸው አካላት ከወዲሁ ሊያመቻችልን ይገባል ብለዋል፡፡

o

Last Updated ( Tuesday, 16 June 2020 11:46 )
 
Print PDF
User Rating: / 3
PoorBest 

በአማራ ክልል በጣና ዙሪያ የሚገኘው የፎገራ ከብት ዝርያ ቁጥሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን ጥናቶች አረጋገጡ፡፡ |etv

Please click here to watch this video on YouTube

 

 
More Articles...
Page 6 of 34
You are here: Home