Frontpage Slideshow | Copyright © 2006-2010 JoomlaWorks, a business unit of Nuevvo Webware Ltd.

Print PDF

 

CALM-P4R ፕሮጀክት ማስጀመሪያ የውይይት መድረክ በእንጅባራ ከተማ ተካሄደ

በውይይት መድረኩ የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር / ጥላዪ ተክለወልድ በመክፈቻ ንግግራቸዉ የተፈጥሮ መመናመን የአገራችን ዋነኛ ችግር እንደሆነ ገልፀዉ ችግሩን ለመፍታት 1977 . ጀምሮ ከፍተኛ ርብርብ እንደተደረገና ሰፊ ስራም ሲሰራ እንደቆየ ጠቅሰዋል፡፡ ይህን ስራ ለመደገፍ ሰፊ የምርምር ስራ መሰራቱን ጠቅሰው ለአብነትም የተቀናጀ የተፋሰስ ስራ ሲሰራ የቆየ ቢሆንም ከቴክኖሎጅ አቅርቦት አንፃር የሚፈለገውን ስራ በበቂ ደረጃ እንዳልተሰራና የተደረጉ ጥረቶች እንዳሉ ሆነዉ ወቅቱን ያገናዘበና ልማቱን ሊያግዝ የሚችል የቴክኖሎጂ ማፍለቅ/ማላመድና ማስተዋወቅ የምርምር ስራዎች እንደሚያስፈልግ ጨምረዉ ገልፀዋል፡፡ ዋና ዳይሬከተሩ አክለዉም የተለያዩ ፕሮጀክቶች በክልላችን የተሻለ የተፋሰስ ስራ የሰሩ ቢሆንም ዘላቂነታቸውና አስተማማኝነታቸዉ ጥያቄ ዉስጥ የሚገባ ነዉ፡፡ ለዚህም ምርምሩ ድግግሞሽን ያስቀረ፤ ሁሉንም የተፋሰስ ልማት አካላት የያዘና ተቋማዊ የሚደረግ (Institutional) እሴት ሊጨምር የሚችልና ቢዝነስ ኦሬንትድ የሆነ፤ “Innovative” የሆነ አካሄድን የተከተለ ተግባር ተኮር ዉጤት የሚያመጣ ምርምር (Action research) መስራት እንደሚገባ አፅዕኖት ሰጠዉ አሳስበዋል፡፡

ምርምሩም ሆነ የልማት አካሉ ግንኙነታቸዉን በማጥበቅ በጋራ ተወያይተዉ፣ አቅደዉና ተግበረዉ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማቱን በማሳለጥ ማህበረሰቡን ተጠዋሚ ማድረግ እንዳለባቸዉ አስገንዝበዋል፡፡ በመጨረሻም ከዚህ የምክክር መድረክ ምርምሩና የልማት አካሉ ማን ምን መስራት አለበት የሚለዉን በቂ ግንዛቤ ይዘዉ ይወጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡ ከአብክመ ግብርና ቢሮ እንዲሁም ከእያንዳንዱ የኢንስቲትዩቱ ማዕከላት CALM-P4R ፕሮጀክት አስተባባሪዎች ዕቅዶቻቸዉንና እስካሁን ያከናወኗቸዉን ተግባራት አቅርበዋል፡፡ በቀረበዉ ላይ አስተያየቶች/ጥያቄዎች/ማሻሻያ ሃሳቦች ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዉ የጋራ መግባባትና ስምምነት ተደርሶባቸው የዕለቱ ዉይይቱ ተጠናቋል፡፡ በውይይት መድረኩ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የቴክኒክ ዳይሬክተሮች፣ የምርምር ማዕከላት ዳይሬክተሮችና የየማዕከላቱ CALM-P4R ፕሮጀክት አስተባባሪዎች እንዲሁም የአብክመ ግብርና ቢሮ CALM-P4R ፕሮጀክት አስተባባሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

128kh128rt128ui

Last Updated ( Monday, 19 July 2021 06:31 )
 
Print PDF
User Rating: / 1
PoorBest 

የሙዝ ሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የወራሚት አትክልትና ፍራፍሬ ምርምርና ስልጠና ንዑስ ማዕከል አስታወቀ

በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ስር የሚገኘው የወራሚት አትክልትና ፍራፍሬ ምርምርና ስልጠና ንዑስ ማዕከል በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች የተሻሻሉ የሙዝ ዝርያዎችን እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡ ንዑስ ማዕከሉ በቆጋ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮች ሙዝን በዘመናዊ መንገድ አልምተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሰራ ሲሆን በፕሮጀክቱ ውስጥ ተጠቃሚ በሆኑ አርሶ አደሮች ማሳ ላይ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የመስክ ቀን ተካሂዷል፡፡

በመስክ ቀኑ በወራሚት አትክልትና ፍራፍሬ ምርምርና ስልጠና ንዑስ የአትክልትና ፍራፍሬ ተመራማሪ አቶ ምንውየለት ጀምበሬ ንዑስ ማዕከሉ አርሶ አደሩ የተሻሻሉ የሙዝ ዝርያዎችን በስፋት አምርቶ ተጠቃሚ እንዲሆን መንደርን መሰረት ያደረገ የሙዝ ልማት ስራ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ በዚህም በክልሉ በ11 ወረዳዎች የሙዝ መንደርን በመመስረት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግና ያለውን የገበያ ፍላጎት ለመሙላት እየተሰራ ነው ያሉት ተመራማሪው 4 ምርታማ ዝርያዎችን (ፓዮ፣ ግራንድካቫዲሽ፣ ቡታዞ እና ዊሊያምስ 1 የተሰኙ) የማስተዋወቅና ስራውን የበለጠ የማስፋት ስራ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ዝርያዎቹ ከአካባቢው ዝርያ ጋር ሲነጻጸሩ ትልልቅ መጠን ያለው የሙዝ ምርት የሚሰጡ፣ የተሻለ ጣዕም ያላቸውና በገበያ ተፈላጊ የሆኑ፣ በአንድ የሙዝ ዛፍ ላይ ከነባሩ ዝርያ በተሻለ ከፍተኛ ምርት የሚሰጡና ጠንካራ ቆዳ ያላቸው በመሆኑ ቶሎ የማይበላሹ ናቸው፡፡

በቆጋ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ውስጥ የተሻሻሉ የሙዝ ዝርያዎችን እያለሙ ከሚገኙ አርሶ አደሮች መካከል አርሶ አደር አበጀ አስማረ በበኩላቸው ከዚህ በፊት ነባሩን የአካባቢ ሙዝ ዝርያ ያለሙ እንደነበር ገልጸው በንዑስ ምርምር ማዕከሉ የቀረቡላቸው የተሻሻሉት ዝርያዎች በፊት ከነበረው የአካባቢ ዝርያ በተሻለ ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በምርምር ተቋሙ የቀረቡት ዝርያዎች በቀላሉ የማይበላሹ፣ ምርታማ እና በገበያ ተፈላጊ መሆናቸውን የጠቀሱት አርሶ አደሩ ስራው በአግባቡ ከተያዘ ተጠቃሚ ስለሚያደርገን በቀጣይም በስፋት እንገባበታለን ብለዋል፡፡

እስካሁን ነባሩን የሙዝ ዝርያ ብቻ እያለሙ የሚገኙና በመስክ ቀኑ የተገኙት ሌላኛው አርሶ አደር ይመር ምስክር አዲሱን የሙዝ ዝርያ ተጠቃሚ ላያደርገኝ ይችላል በሚል ተጠራጥሬው የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ብዙ ጥቅም የሚሰጥ መሆኑን ስለተረዳሁ በቀጣይ የተሻሻሉ የሙዝ ዝርያዎችን ለማልማት ዝግጁ ነኝ በማለት ተናግረዋል፡፡

የወራሚት አትክልትና ፍራፍሬ ምርምርና ስልጠና ንዑስ ማዕከል በክልሉ ብቸኛው የአትክልትና ፍራፍሬ የምርምር እና ስልጠና ን/ማዕከል ሲሆን በቀጣይ ወደ ማዕከልነት በማደግ በዘርፉ ክልሉን የበለጠ ይጠቅማል ተብሎ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ን/ማዕከል ነው፡፡

b373

 

b273

 

Last Updated ( Thursday, 24 June 2021 13:57 )
 
Print PDF
User Rating: / 1
PoorBest 

የምርምር_ምክረ_ሀሳቦች

#የናይትሮጅን_የፎስፈረስ_የፖታሲዬም_እና_የሰልፈር_ንጥረ_ነገሮች_አስፈላጊነት_ጥናት_ውጤት

#ለጤፍ_ሰብል

 #ናይትሮጂን፣ ለጤፍ ሰብል በጃማ በሄክታር 69 ኪ.ግ. ናይትሮጂንና 46 ኪ.ግ. ፎስፈረስ (P2O5) መጨመር ማዳበሪያ ካልተጨመረበት ጋር ሲወዳደር የ5 ኩ/ል የምርት ብልጫ ያሳየ ሲሆን ከዚህ በላይ መጨመር ጉልህ የሆነ የምርት ጭማሪ እንደማያስገኝ የጥናቱ ውጤት ያሳያል፡፡ የፖታሺየም እና ሰልፈር ንጥረ ነገሮች ለአካባቢው ከተመከረው ማዳበሪያ መጠን የተሻለ የምርት ጭማሪ አላስገኙም፡፡

 #በደልጊ ለጤፍ #በፖታሺየምና #በሰልፈር ማዳበሪያ ተጠቃሚ ተጠኚዎች መካከል የምርት ልዩነት ያልታየ ሲሆን በናይትሮጂንና በፎሰፎረስ ተጠኚዎች መካከል ግን ልዩነት ታይቷል፡፡ በመሆኑም 69 ኪ/ግ ናይትሮጂን በሄ/ር ለጤፍ መጨመር 17.24 ኩ/ል በሄ/ር ኢኮኖሚያዊ አዋጭነት ያለው ምርት አስገኝቷል፡፡ ይህም ሌሎች ንጥረ ነገሮች ተጨምረው ናይትሮጂን ብቻ ካልተጨመረበት ተጠኝ የ7.6 ኩ/ል ወይም 78.8% ምርት ብልጫ ሲያስገኝ፣ 161 ኪ.ግ. ናይትሮጂንና ሌሎች ንጥረ ነገሮች ከተጨመሩበት ጋር ሲነጻጸር ደግሞ የጎላ ምርት ልዩነት አላሳየም፡፡ በተመሳሳይ 46 ኪ/ግ ፎስፎረስ (P2O5) በሄ/ር ለጤፍ መጨመር 16.6 ኩ/ል የጤፍ ምርት በሄ/ር ያስገኘ ሲሆን ይህም ኢኮኖሚያዊ አዋጭነት ያለው ምርት ነው፡፡ ይህም ሁሉም ንጥረ ነገሮች ተጨምረው ፎስፈረስ ብቻ ካልተጨመረበት ተጠኚ የ10% ምርት ጭማሪ ሲያስገኝ 115 ኪ.ግ ፎስፈረስ (P2O5) ከተጨመረበት ተጠኝ ግን የጎላ የምርት ልዩነት የለውም፡፡ በመሆኑም ለጤፍ ምርት ጭማሪ ናይትሮጂንና ፎስፈረስ (P2O5) ንጥረ ነገሮች አስፈላጊ መሆናቸውን ፖታሲየምና ሰልፈር ለጊዜው እንደማያስፈልጉ ተረጋግጧል፡፡

 #በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ለቡናማ አፈርና ለጥቁር አፈር ዓይነቶች ኢኮኖሚያዊ አዋጪ እና የተሻለ የጤፍ ምርት (18 ኩ/ል በሄ/ር) ያስገኘው የ46 ኪ.ግ. #ናይትሮጂንና የ46 ኪ.ግ. #ፎስፎረስ (P2O5) ጥምረት ነው፡፡ ይህም ምንም ካልተጨመረበት ማሳ በሄ/ር ከተገኘው ስምንት ኩ/ል ምርት ጋር ሲነጻጸር የ10 ኩ/ል ወይም የ125% ምርት ብልጫ አለው፡፡ በመሆኑም ለጎንደር ዙሪያና ተመሳሳይ ቡናማና ጥቁር አፈር አካባቢዎች 46 ኪ.ግ. ናይትሮጂንና 46 ኪ.ግ ፎስፈረስ (P2O5) መጠቀም ይመከራል፡፡

 

የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በ2013ዓ.ም 7 አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችን አስለቀቀ

 

ምርምር ኢንስቲትዩቱ በስሩ በሚገኙ የምርምር ማዕከላት አማካኝነት 7 የሰብል ዝርያዎችን ማስለቀቁን በኢንስቲትዩቱ የሰብል ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አለማየሁ አሰፋ ገልጸዋል፡፡

በዚህም የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል አዲስ የብቅል ገብስ ዝርያ ያስለቀቀ ሲሆን ዝርያው በሀገሪቱ ካሉት የብቅል ገብስ አይነቶች የተሻለ ጥራት ያለውና ምርታማ ነው፡፡ ዝርያው ቢራ ፋብሪካዎች የሚፈልጉትን ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ማሟላቱ የተረጋገጠ ሲሆን ከዚህ በፊት ከነበሩት ባለ ሁለት ጠርዝ የብቅል ገብስ ዝርያዎች በተለየ 6 ጠርዝ ያለው ነው፡፡ አሁን ላይ በአማራ ክልል አርሶ አደሮች ከሚያመርቱት IBON-174/03 ከተሰኘው ዝርያ ጋር ሲነጻጸርም የ13.6 በመቶ የምርት ጭማሪ አለው፡፡ ይህም በአማካኝ እስከ 50 ኩንታል በሄክታር ምርት መስጠት የሚችል ሲሆን የብቅል ገብስን የሚያጠቁ በሽታዎችን የመቋቋም አቅሙም ከፍተኛ ነው፡፡

ሌላው በደብረብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል አዲስ የባቄላ ዝርያ ተለቋል፡፡ ዝርያው ከዚህ በፊት በምርታማነታቸው ከሚታወቁ ዝርያዎች ጋር ሲነጻጸር ተቀራራቢ ምርት የሚሰጥ ሲሆን ከሌሎች ጋር ሲነጻጸር ትልልቅ ፍሬ ያለው በመሆኑ የውጭ ገበያን ትኩረት የሚስብ፣ በደጋማ አካባቢዎች በስፋት መመረት የሚችልና በሽታ የመቋቋም አቅሙም በአንጻራዊነት የተሻለ የሆነ ዝርያ ነው፡፡ ይህ ዝርያ ጥቁር አፈር ባላቸው አካባቢዎችና በደጋማ ቦታዎች የሚመረት መሆኑ የተሻለ ያደርገዋል፡፡ ዝርያው በአማካኝ እስከ 39 ኩንታል ምርት በሄክታር የመስጠት አቅም አለው፡፡ ኢንስቲትዩቱ አዲስ የባቄላ ዝርያ ሲያስለቅቅ ከ1997ዓ.ም ወዲህ የመጀመሪያው ነው፡፡

በ2013ዓ.ም የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል አዲስ የጤፍ ዝርያ ያስለቀቀ ሲሆን ዝርያው ከአሁን በፊት አርሶ አደሩ ከሚጠቀመው “አባይ” የተሰኘ የጤፍ ዝርያ ጋር ሲነጻጸር የ10 በመቶ የምርት ጭማሪ ያለው ሲሆን ጣቁሳ አካባቢ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ከሚገኘው “ጸደይ” የተሰኘ ዝርያ ደግሞ የ31.3 በመቶ የምርት ጭማሪ አለው፡፡ ዝርያው ነጭ ቀለም ያለው እና ፈጥኖ የሚደርስ መሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል፡፡ በተለይም ቀድሞ የሚደርስ መሆኑ ጥቁር አፈር ባላቸውና እርጥበትን ይዘው በሚቆዩ አካባቢዎች የጤፉ ሰብል ከተሰበሰበ በኋላ ሌሎች ሰብሎችን ለመዝራት እድል የሚፈጥር ነው፡፡

የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል አዲስ የሽንብራ ዝርያም አስለቅቋል፡፡ ዝርያው በስፋት ጥቅም ላይ ከሚውለው “ዲምጡ” ከተሰኘው ዝርያ ጋር ሲነጻጸር የ28.18 በመቶ የምርት ጭማሪ ያለው ወይም 21.12 ኩንታል ምርት በሄክታር መስጠት የሚችል ነው፡፡ ዝርያው ቀይ ቀለም ያለው፣ ሽንብራን የሚያጠቁ በሽታዎችን በአንጻራዊነት መቋቋም የሚችል፣ በገበያ ተፈላጊ እና ወደ ውጭ የሚላኩ የሽንብራ ምርቶችን ደረጃ ያሟላ ዝርያ መሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል፡፡

የሲሪንቃ ግብርና ምርምር ማዕከል ደግሞ አዲስ የቦሎቄ ዝርያ አስለቅቋል፡፡ ዝርያው 27.29 ኩ/ል በሄክታር መስጠት የሚችልና የተሻለ ምርት አለው ተብሎ ከሚታሰበው “አዋሽ 2” ከተሰኘው ዝርያ የ23.6 በመቶ የምርት ጭማሪ ያለው ነው፡፡ በሽታና ድርቅ የመቋቋም አቅሙ የተሻለ በመሆኑ ተመራጭ ሊሆን የሚችል ዝርያ ነው፡፡

አዲስ የአተር ዝርያም በአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል ተለቋል፡፡ ዝርያው ከዚህ በፊት ከሚታወቀው “ተሻለ” ከተሰኘው የአተር ዝርያ ጋር ሲነጻጸር የ21.76 በመቶ የምርት ብልጫ ያለውና በአማካኝ 23.17 ኩ/ል ምርት በሄክታር የሚሰጥ ነው፡፡ ነጭ ቀለም ያለው፣ በአርሶ አደሮች ግምገማ ተመራጭ ዝርያ መሆኑና ከምስር ጋር እኩል ጠቀሜታ ያለው ሊሆን እንደሚችልም አርሶ አደሮች ተናግረዋል፡፡

በአትክልትና ፍራፍሬ ሰብሎች በኩል የደብረ-ብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል እጅግ ምርታማ የሆነ አዲስ የነጭ ሽንኩርት ዝርያ አስለቅቋል፡፡ ዝርያው ከአካባቢው የሽንኩርት ዝርያ የ40% የምርት ጭማሪ ያለው ወይም 130.3 ኩንታል ምርት በሄክታር መስጠት የሚችል ነው፡፡ ዝርያው ትልልቅ መጠን ያለው፣ ሙሉ ነጭ የሆነ፣ በሽታ የመቋቋም አቅሙ የተሻለ እና በከፍተኛ ቦታዎች አካባቢ መላመድ የሚችል ዝርያ ነው፡፡ የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አዲስ የነጭ ሽንኩርት ዝርያ ሲያስለቅቅ የመጀመሪያው መሆኑንም ዶ/ር አለማየሁ አሰፋ ተናግረዋል፡፡ዝርያዎቹ ወደ አርሶ አደሩ ወርደው የተሻለ ጥቅም እንዲሰጡ የአራቢ ዘር የማባዛት፣ የማስተዋወቅና የቅድመ-ማስፋት ስራዎች በስፋት እንደሚሰሩ ዶ/ር አለማየሁ ገልጸዋል፡፡

ce123

 

Last Updated ( Thursday, 24 June 2021 13:47 )
 
Print PDF
User Rating: / 1
PoorBest 

በምርታማነታቸው በምርምር የተለዩ የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ-አደሩ በማስተዋወቅ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል የተሻለ ምርት የሚሰጥ “አዳማ ሬድ” የተባለ የቀይ የሽንኩርት ዝርያን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኪንፋዝ በገላ ወረዳ አድርቀይና ቀበሌ የመስኖ አዉታር ተጠቃሚ ለሆኑ አርሶ-አደሮች በማቅረብ እና ሙያዊ እገዛ በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሰራ ይገኛል፡፡ የስራውን እንቅስቃሴ ተመልክቶ ተሞክሮውን የበለጠ ለማስፋትም በቀበሌው የመስክ ቀን ተካሂዷል፡፡ በመስክ ቀኑ የእድሉ ተጠቃሚ የሆኑ አርሶ አደሮች በምርምር ማዕከሉ የቀረበላቸውን የሽንኩርት ዘር በመጠቀም በ2012 ዓ/ም የተሻለ ተጠቃሚ እንደነበሩ ገልፀው በዚህ ዓመት ግን ባለው የገበያ ሁኔታ ተጠቃሚ እንዳልሆኑ ገልጸዋል፡፡ የገበያ ትስስር ስላልተፈጠረልን በድካማችን ልክ ተጠቃሚ አልሆንም ያሉት አርሶ አደሮቹ የምርምር ማዕከሉን በማመስገን ሌሎች የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችም እንዲቀርቡላቸው ጠይቀዋል፡፡

በጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል የአፈር ምርምር ተመራማሪ አቶ አትክልት አበራ ማዕከሉ በህዝቡ ጥያቄና ፍላጎት መሰረት ለአካባቢዉ ስነ-ምህዳር ተስማሚ የሆኑ የሰብል አይነቶችን እየለየ እንደሚያስተዋውቅ ገልጸው አካባቢዉ ዝናብ አጠር በመሆኑ የአርሶ-አደሩን የምግብ ዋስትና የሚያረጋግጡ ውጤታማ የሰብል ዝርያዎችን በቀጣይ እንደሚያቀርብ ተናግረዋል፡፡ አርሶ-አደሩም በምርምር ማዕከሉ ለትዉዉቅ የሚቀርቡለትን ዝርያዎች በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ተመራማሪው አስገንዝበዋል፡፡ ከዚህ በፊት ከቀይ ሽንኩርት በተጨማሪ ምርምር ማዕከሉ የቲማቲም እና የሀብሃብ ዝርያዎችን አቅርቦ እንደነበር ያስታወሱት አቶ አትክልት ነገር ግን ዝርያዎቹን ተቀብሎ ወደ ስራ የገባው አርሶ አደር ቁጥር ትንሽ ነው ብለዋል፡፡ ይህ መስተካከል እንዳለበት የጠቆሙት ተመራማሪው ምርምር ማዕከሉ መነሻ ዘር እንደሚያቀርብ ገልጸው አሁንም ለ5 ሄክታር የሚሆን ምርታማ የሆነ የጤፍ ዘር እናስረክባለን ብለዋል፡፡ በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአፈርና ዉሃ ጥበቃ ተመራማሪ ዶ/ር ሀይሉ ክንዴ በበኩላቸው አርሶ አደሩ የቴክኖሎጅ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚደረገው ክትትልና ድጋፍ ጅምሩ ጥሩ መሆኑን ገልጸው አርሶ አደሩ ላይ የሚታየው የማሳ አያያዝ ክፍተት መስተካከል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ አርሶ-አደሩ የሚፈልገውን የምርት መጠን ለማግኘት ማሳውን በወቅቱ ማረምና መንከባከብ እዳለበት በማሳሰብ በጥያቄአችሁ መሰረት የተሻሻሉ ዝርያዎች ወደ አርሶ አደሩ እንዲደርሱ ኢንስቲትዩቱ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

t12t534tr35te53532

 

 

Last Updated ( Thursday, 24 June 2021 13:39 )
 
More Articles...
Page 2 of 34
You are here: Home