Frontpage Slideshow | Copyright © 2006-2010 JoomlaWorks, a business unit of Nuevvo Webware Ltd.

Print PDF
User Rating: / 1
PoorBest 

የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የተገዙ ዘመናዊ የአፈር ማከሚያ ማሽኖች ተረከበ፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከበሽታ ነጻ የአትክልትና ፍራፍሬ ዘር ለማምረት የሚያስችለው ማሽን በወርድ ቪዥን ኢትዮጵያ በኩል የተገዛ ሲሆን በኢንስቲትዩቱ ዋና መስሪያ ቤት የወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ኤድዋርድ ብራውን በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል፡፡ የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጥላዬ ተክለወልድ ኢንስቲትዩቱ ከበሽታ ነጻ የሆኑ የአትክትልና ፍራፍሬ ዘሮችን ለክልሉ አርሶ አደሮች ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸው ከበሽታ ነጻ የሆነ ዘር ለማምረት የሚያግዙ ዘመናዊ ቴክኖሎጅዎችን ለማሟላት ኢንስቲትዩቱ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም ኢንስቲትዩቱ ከወርድ ቪዥን ኢትዮጵያ ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት ሀገር ውስጥ ገበያ ላይ የማይገኙ 2 ዘመናዊ የአፈር ማከሚያ ማሽኖች በ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር ወጭ ተገዝተው ተረክበናል ያሉት ዶ/ር ጥላዬ ወርድ ቪዥን ኢትዮጵያ የድንች ዘር ቀጥታ እንድንሸጥለት ጠይቆን የነበረ ቢሆንም እኛ ግን ተቋሙን በዘመናዊ መሳሪያዎች ማደራጀት ስለፈለግን የድንች ዘሩን ዋጋ ቀጥታ ከሚከፍለን የአፈር ማከሚያ ማሽን እንዲገዙልን በጠየቅናቸው መሰረት ሁለቱን ማሽኖች ገዝተው አስረክበውናል ብለዋል፡፡ ማሽኖቹ ውድ ከመሆናቸው በላይ በሀገር ውስጥ ገበያ የማይገኙና የውጭ ምንዛሬን የሚጠይቁ በመሆናቸው በወርል ቪዥን በኩል ቀጥታ ተገዝተው መምጣታቸው ለኢንስቲትዩቱ ትልቅ አጋጣሚ መሆኑንም ዶ/ር ጥላዬ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በፊት በተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማትና ፕሮጀክቶች ጋር በሚደረጉ የትብብር ስምምነቶች የሚገኙ የገንዘብ ድጋፎችን ኢንስቲትዩቱ በዋናነት ተቋሙ የምርምር ስራውን በብቃት ለመፈጸም የሚያስችሉ ዘመናዊ መሳሪያዎችን ለማሟላት እየተጠቀመባቸው መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤርሚያስ አባተ ወርልድ ቪዥን ስላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልጸው አጠቃላይ ኢንስቲትዩቱ ደረጃውን የጠበቀ ዘር ለማምረት እያከናወናቸው ስላሉ ተግባራትና የምርምር ስራዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡ የወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ኤድዋርድ ብራውን በበኩላቸው ከአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር ተባብረው መስራታቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸው በቀጣይ ወርድ ቪዥን ከኢንስቲትዩቱ ጋር ተባብሮ ይሰራል ብለዋል፡፡

730062 n307715 n294 n

Last Updated ( Thursday, 03 June 2021 14:27 )
 
Print PDF
User Rating: / 1
PoorBest 

የአንዳሳ እንስሳት ምርምር ማዕከል የእንስሳት ዝርያን ከማሻሻልና ከመጠበቅ ጎን ለጎን ለዝርያ መሻሻልና ምርታማነት መጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክተው መኖ ልማት ላይም የምርምር እና የብዜት ስራ እያከናወነ ነው፡፡ ለስራው ውጤታማነትም በAGP 2 ድጋፍ ዘመናዊ የመስኖ አውታር አስገንብቶ ስራ አስጀምሯል፡፡

ቪዲዮውን ይመልከቱ!

የፎገራ ከብት ዝርያን ለማሻሻልና ለመጠበቅ በአንዳሳ እንስሳት ምርምር ማዕከል ግቢ ውስጥ የተወለዱ ጥጆች

ቪዲዮውን ይመልከቱ!

የአንዳሳ እንስሳት ምርምር ማዕከል የፎገራ ከብት ዝርያን ለማሻሻል እያከናወናቸው የሚገኙ የምርምር ስራዎች

ቪዲዮውን ይመልከቱ!

ከዚህ በፊት ኢንስቲትዩታችን የአፍሪካ ኦስትሪያ የምርምር ተቋማት ጥምረት Austrian-African Research Network | Africa-UniNet አባል መሆኑን ገልጸንላችሁ ነበር፡፡ አሁን ጥምረቱ ይፋዊ የአባልነት የምስክር ወረቀት ሰጥቶናል፡፡

 

09468333 n

በአንዳሳ እንስሳት ምርምር ማዕከል እየተከናወኑ የሚገኙ የምርምር ስራዎች በክልሉ የስራ ኃላፊዎች ተጎበኙ::

የአንዳሳ እንስሳት ምርምር ማዕከል በዋናነት የእንስሳት ዘርፉን ለማሻሻል ዋና ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ማዕከል ሲሆን ምርምር ማዕከሉ እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የእንስሳት ምርምር ስራዎች በባለድርሻ እና አጋር አካላት ተጎብኝተዋል፡፡ ምርምር ማዕከሉ የክልሉን የዶሮ ፍላጎት ለማሟላት እያከናወነ ያለው ዘመናዊ የዶሮ ምርምር እና ብዜት ፋሲሊቲ በባለድርሻ አካላት ምልከታ ተደርጎበታል፡፡ የዶሮ ምርምር እና ብዜት ጣቢያው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በአንዴ ከ74ሺህ 800 በላይ ጫጩቶችን የማስፈልፈል አቅም አለው፡፡ በምርምር እና ብዜት ጣቢያው የስጋና እና የእንቁላል ምርት የሚሰጡ የተሻሻሉና የውጭ ዝርያ ያላቸው ኮክኮክ የተሰኙ ዶሮዎች ምርምር እና ብዜት፣ የሀገረሰብ ዝርያ የሆነው የቲሊሊ ዶሮ ማሻሻል የምርምር ስራዎች፣ ዥግራን የማላመድ እና የንጥረ ምግብ ይዘቱን የማጥናት የሙከራ ስራዎች አና ሌሎች መሰረተ-ልማቶች ተጎብኝተዋል፡፡ ሀገር በቀል የሆነው የፎገራ ከብት ዝርያን ለማሻሻል እየተሰሩ የሚገኙ የምርምር ስራዎች፣ በማዕከሉ የሚገኘው ዘመናዊ የመኖ ማቀነባበሪያ ማሸን ያለበት ደረጃ፣ በማዕከሉ አቅራቢያ የሚገኘው የመደቢት ዘመናዊ የመስኖ አውታርና የተሻሻሉ የመኖ ዝርያዎች የምርምር እና የብዜት ስራዎች ከተለያዩ ተቋማት በተወጣጡ የስራ ኃላፊዎች ምልከታ ተደርጎባቸዋል፡፡ 

በመስክ ምልከታው የተገኙት የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጥላዬ ተክለወልድ የእንስሳት ዘርፉ በአግባቡ ቢሻሻል በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ሊኖረው የሚችለውን ጠቀሜታ ካብራሩ በኋላ የአንዳሳ የእንስሳት ምርምር ማዕከል ዘመናትን ያስቆጠረ ማዕከል መሆኑንና ለክልሉ የእንስሳት ዘርፍ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ የሚገኝ ተቋም እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ማዕከሉ በሚገባ ባለመደገፉ የእድሜውን ያክል እየሰራ እንዳልሆነ የጠቀሱት ዶ/ር ጥላዬ ባለድርሻ እና አጋር አካላት ማዕከሉ የሚጠበቅበትን ስራ እንዲሰራ የማጠናከር እና የመደገፍ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መለስ መኮንን በበኩላቸው ማዕከሉ እያከናወናቸው የሚገኙ የምርምር እና የብዜት ስራዎች ጥሩ መሆናቸውን ገልጸው ማዕከሉ የሚጠበቅበትን ተልዕኮ በተሟላ መንገድ እንዲፈጽምና የክልሉን የእንስሳት ሀብት ዘርፍ በማሻሻል በኩል ትርጉም ያለው ውጤት እንዲያስመዘግብ ሁላችንም በምንችለው ሁሉ መደገፍ ይገባናል ብለዋል፡፡

a1194514256a3673 n

የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የምርምር ማዕከላትና የኢንስቲትዩቱ የጋራ የስራ ግምገማ(ኤክስቴንድድ ማኔጅመንት) ተካሂዷል፡፡

በኢንስቲትዩቱ ስር የሚገኙ ሁሉም የምርምር ማዕከላትና ንዑስ ማዕከላት የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት በበጀት አመቱ እስካሁን የተሰሩ ሁለንተናዊ ስራዎች በባህር ዳር ከተማ በኢንስቲትዩቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግምገማው ተካሂዷል፡፡ በግምገማው በተልዕኮ አፈጻጸም፣ በሀብት አጠቃቀም፣ በሪፎርም አተገባበር፣ ከአጋር አካላት ጋር ያለው ግንኙነት፣ በ ክትትልና ግምገማ፣ በመስኖ ስራዎች አፈጻጸም፣ በማዕከላት ልማት ስራዎች፣ በመረጃ አያያዝ፣ በየመልካም አስተዳደር ችግሮች አፈታት እና በማህበራዊ ግንኙነትና ተግባቦት በኩል እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በዝርዝር ተገምግመዋል፡፡ በተጨማሪም ከምርምር ስራዎች ጎን ለጎን ኮሮናን በመከላከል ረገድ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እና ወቅታዊ የጸጥታ ችግሮችን ተቋቁሞ መደበኛ የምርምር ስራዎችን ከመፈጸም አኳያ ያሉ ጥንካሬዎችና ድክመቶች ተለይተው ግምገማ ተደርጎባቸዋል፡፡ በቀጣይ መሰራት ያለባቸውን ዋና ዋና ተግባራት በተመለከተም ውይይት የተደረገ ሲሆን በኢንስቲትዩቱ የስራ ኃላፊዎች አማካኝነት የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ በተለይ የኮሮና ቫይረስን በመከላከልና ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታዎችን በንቃት በመከታተል ኢንስቲትዩቱ መደበኛ ስራዎቹ እንዳይስተጓጎሉ በትጋት መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

6765-0975gdsas

የናይትሮጅን የፎስፈረስ የፖታሲዬም እና የሰልፈር ንጥረ ነገሮች አስፈላጊነት ጥናት ለስንዴ

ናይትሮጂን፡- በፋርጣና በወንበርማ ወረዳዎች ከፍተኛ የስንዴ ምርት የተገኘው ከ222 ኪ.ግ ናይትሮጂን በሄክታር ሲሆን የተገኘው ምርት በፋርጣ 44.2 ኩ/ል በሄ/ር እና በወንበርማ ደግሞ 46.8 ኩ/ል በሄ/ር ነው፡፡ ይኸውም 92 ኪ.ግ ናይትሮጂን ከተጨመረበት ተጠኝ ያለው የምርት ብልጫ በፋርጣ የ34.34% እና በወንበርማ የ17.3% ነው፡፡ በባሶና_ወራና (በጉዶበረትና ጎሸባዶ) ከፍተኛ የስንዴ ምርት የተገኘው ከ222 ኪ.ግ ናይትሮጂን በሄ/ር ሲሆን በጎሸባዶ ለአካባቢው ከተመከረው የማዳበሪያ መጠን የ20.5% ምርት ብልጫ እንዲሁም በጉዶበረት የ28.6% ምርት ብልጫ አስገኝቷል፡፡ ይህ የሚያሳየው ናይትሮጂን ለስንዴ ምርት ጭማሪ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያለው መሆኑን ነው፡፡

ፎስፈረስ፡- በፋርጣ እና ተመሳሳይ አካባቢዎች ለስንዴ ፎስፈረስን(P2O5) መጨመር የምርት ልዩነት አላሳየም፡፡

በወንበርማ እና ተመሳሳይ አካባቢዎች ግን ፎስፈረስ (P2O5) ከፍተኛ የምርት ጭማሪ እንዳስገኘ ታይቷል፡፡ በዚህ መሠረት ከፍተኛ ምርት (47.9 ኩ/ል/ ሄክታር) የተገኘው ከ115 ኪ.ግ ፎስፈረስ (P2O5) በሄ/ር ነው፡፡ ይኸውም 69 ኪ.ግና 92 ኪ.ግ P2O5 በሄ/ር ከተጨመረባቸው የ19.75%ና 19.45% ምርት ብልጫ በቅደም ተከተል አስገኝቷል፡፡ በበባሶና_ወረና በጎሽባዶ እና ተመሳሳይ አካባቢዎችም ከፍተኛ ምርት የተገኘው ከ115 ኪ.ግ. ፎስፈረስ (P2O5) በሄ/ር ሲሆን ለአካባቢው ከተመከረው የማዳበሪያ መጠን ጋር ሲነጻጸር የ9.4% ምርት ብልጫ አስገኝቷል፡፡ በተመሳሳይ ወረዳ በጉዶበረት ደግም ከፍተኛ ምርት የተገኘው ከ69 ኪ.ግ. ፎስፈረስ (P2O5) በሄ/ር ሲሆን ለአካባቢው ከተመከረው የማዳበሪያ መጠን ጋር ሲነጻጸር የ4.6% ምርት ጭማሪ በሄ/ር አስገኝቷል፡፡ በመሆኑም ፎስፈረስን መጨመር በስንዴ ምርት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጓል፡፡

ፖታሲየም፡- በሁሉም አካባቢዎች (በወንበርማ፣ ፋርጣ፣ በጎሸባዶና በጉዶ በረት) ፖታሲየም በምርት ጭማሪ ላይ የጎላ ልዩነት አላሳየም፡፡ በመሆኑም ፖታሲየምን መጠቀም አርሶ አደሮችን ትርፋማ አያደርግም፡፡ ሰልፈር፡ በፋርጣና ተመሳሳይ አካባቢዎች ሰልፈር በስንዴ ምርት ላይ የጎላ የምርት ልዩነት ያላሳየ ሲሆን በወንበርማና ተመሳሳይ አካባቢዎች ግን የምርት ልዩነት አሳይቷል፡፡ በመሆኑም በወንበርማ ከፍተኛ ምርት (48 ኩ/ል በሄ/ር) የተገኘው 40 ኪ.ግ ሰልፈር (S) እና የተመከሩ ሌሎች ንጥረ ነገሮች በሄ/ር ከተጨመረበት ማሳ ነው፡፡ ይህም 20 ኪ.ግና 50 ኪ.ግ ሰልፈር (S) በሄ/ር እና የተመከሩ ሌሎች ንጥረ ነገሮች ከተጨመረባቸው ማሳዎች የ16.6%ና 9.6% ምርት ጭማሪ በቅደም ተከተል አስገኝቷል፡፡ በጎሸባዶም ሰልፈር በስንዴ ምርት ላይ ምንም ጭማሪ ያላስገኘ ሲሆን በጉዶበረት ግን 10 ኪ.ግ. ሰልፈር (S) በሄ/ር የተጨመረበት ማሳ ከፍተኛ የስንዴ ምርት አስገኝቷል፡፡ ይህም ለአካባቢው ከተመከረው የማዳበሪያ መጠን ጋር ሲነጻጸር 14.3% ምርት ጭማሪ እንዳላቸው አስገኝቷል፡፡ በመሆኑም በፋርጣ ወረዳና ባሶና ወራና ጎሸባዶ አካባቢ ሰልፈር መጨመር አስፈላጊ አለመሆኑንና ለወንበርማ ወረዳና ለባሶና ወራ ጉዶበረት አካባቢ ሰልፈር መጨመር አስፈላጊ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

 

Last Updated ( Thursday, 03 June 2021 12:55 )
 
Print PDF
User Rating: / 2
PoorBest 

Preparatory Work for Implementation of InnoFoodAfrica Project by ARARI

About InnoFood Africa Project: InnoFood Africa (IFA) is a project aiming to improve farming and primary production practices of African food systems by 1) increasing food diversity by promoting sustainable, climate-smart crop production and post-harvesting practices, 2) boosting productivity and marketability of selected cereals, pulses as well as a root crop by supporting smallholder farmers increase healthy food supply in quantity, quality and diversity and 3) supporting small-scale farmers (especially women and youth) in rural areas to utilize appropriate post-harvest handling and storage technologies of crops including biomass recycling to meet national, regional and international quality standards. InnoFood Africa project is being implemented in four African countries, namely, Ethiopia, Kenya, Uganda, and South Africa since August 2020.

Recent activities through ARARI: The Amhara Agricultural Research Institute (ARARI) has signed a grant agreement with InnoFood Africa to undertake different activities for improving farming practices, seed systems, and product development from the technologies that will be tested and promoted in 2020/21. With respect to improving farming practices, participatory variety selection (Tef, Fababean, and Sweet potato) and participatory technology evaluation (Maize) research activities will be executed in the coming main cropping season at Jigayelmdar and Gashana Akayta kebeles of Jabitehnan and Banja woredas, respectively.

Need assessment: Focus group discussion was conducted with 11 participant farmers separately in two kebeles in Banja and Jabitehnan woredas. Major guiding questions posed for group discussants of FGD were: the types of crops grown, and their average productivity, their biomass yield; the major production constraints, marketing; land preparation, sowing, and other agronomic practices, seed sources, etc. The write-up of the findings will be finalized soon.

Farm/farmer selection and training: Conversant to this, as a preparatory work, a team of researchers from Cereals, Pulses, and Horticultural Crops Case Teams and Socioeconomics and Agricultural Extension Research Directorate have ensured the suitability of the selected sites for the aforementioned on-farm experiments and have also selected 60 farmers as members of farmers’ participatory research (FPR) group. Of these, 18 host farmers who are progressive and have adequate land for FPR have been chosen to accommodate the trials. Given this, 60 farmers, Experts, and Development Agents drawn from Jabitehnan and Banjaworedas and Jigayelmdar and Gashana Akayta kebele Agricultural Development Offices have been trained on tef, maize, faba bean, and sweet potato production and post-harvest management and the roles and usefulness of farmers participatory research (FPR) groups on the 22nd and 24th April 2021.

 

In the training forums, heads of the two woreda Agricultural Development Offices have made an opening speech where they pointed out that this project activity is going to be implemented with lots of expenses to benefit farmers. Thus, farmers need to be attentive in the training, take notes and ask questions that they are not clear with. Besides, they underscored that farmers must prepare the land in time, conduct planting and other agronomic practices on time as per the training and the direction given by the researchers. They also underlined the usefulness of collaboration between research and extension for the success of development and research endeavors. Banja woreda is one of the woredas where crop productivity is declining because of high soil acidity, depleted soil fertility, shortage of improved technologies. Faba bean production and coverage have been decreasing year after year because of gall disease. Therefore, the activity to be executed as participatory faba bean variety selection (PVS) is well-considered and appreciated by the woreda Agricultural Development Office. Conversant to this, a lot of work is expected from the Extension to jointly work with the Research from land preparation to harvesting. The extension will be very much committed to further scale up the faba bean and tef technologies after having seen their performances/results.

Acquisition of seed: Furthermore, the purchase and collection of some different varieties (technologies) of maize such as BH-546, BH-549, BH-661, and Limu has been made from Amhara Seed Enterprise and Melkamu Minichil Agricultural Inputs Supply Organization. Limu is received from the latter free of charge as an expression of commonality to the institute and the poor farmers who are going to benefit from the project activities.

92w7

 

dhgjsdgh73663sgsrw9

 

 

Last Updated ( Friday, 07 May 2021 15:55 )
 
Print PDF
User Rating: / 1
PoorBest 

GIZ ኢትዮጵያ የደብረብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል የምርምር ሙከራ እና ዘር ብዜት ማሳን የማስተካከል(Land leveling) ተግባር አከናወነ

የደብረ ብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር ማዕከሉ ውስጥ የሚገኘው የሙከራ እና የዘር ብዜት ማሳ የመሬቱ አቀማመጥና ለምነቱ ለምርምር ስራ አስቼጋሪ ሆኖበት ቆይቷል፡፡ይህን ችግር ለመቅረፍ GIZ-SSAP (Supporting Sustainable Agricultural Productivity (GIZ-SSAP) የተሰኘ ፕሮጀክት በማዕከሉ ውስጥ የሚገኘውን 12 ሄክታር የሙከራና የዘር ብዜት ማሳ ሙሉ ወጭውን በመሸፈን ማሳውን በማሳስተካከል ለምርምር ስራ ምቹ እንዲሆን አድርጓል፡፡ይህም ምርምር ማዕከሉ በቀጣይ በተለያዩ ሰብሎች ላይ ለሚያከናውናቸው የምርምር ስራዎች ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ የደብረብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር አዳሙ ሞላ GIZ ኢትዮጵያ ለምርምር ማዕከሉ ላደረገው ድጋፍ በማዕከሉ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

901259847410102935

Last Updated ( Tuesday, 27 April 2021 14:04 )
 
More Articles...
Page 3 of 34
You are here: Home