Frontpage Slideshow | Copyright © 2006-2010 JoomlaWorks, a business unit of Nuevvo Webware Ltd.

Print PDF
User Rating: / 2
PoorBest 

 

ኢንስቲትዩቱ ኤክስቴንድድ ማናጅመንት ዓመታዊ ስብሰባ አካሄደ


የአማራ ግብርና ምርምር ኢንሰቲትዩት እና በሥሩ የሚገኙ የምርምር ማዕከላት የማናጅመንት አባላት በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ የኢንስቲትዩቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ አካሂደዋል፡፡

የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጥላዩ ተ/ወልድ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የዚህ ስብሰባ ዓላማ ችግሮችን አንስተን የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ፣ በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ሥራዎችን በጥልቀት ለመገምገም፣ በማዕከላት የተከናወኑ የተሻሉ አሰራሮችን ተሞክሮ መቀያየር፣ የጋራ የሆነ ግንዛቤ መያዝ እና የምርምር ሥራዎችን ለማሳደግ ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦችን ማንሸራሸር ነው ብለዋል፡፡

በስብሰባው ሁሉም የምርምር ማዕከላት እና የኢንስቲዩቱ ቴክኒካል ዳይሬክተሮች ዝርዝር የሆነ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን የምርምር ዳይሬክተሮች በሪፖርታቸው ስለ ምርምር ማዕከላቸው የመሠረተ ልማት ግንባታ የሰው ኃይል ስምሪት፣ የምርምር ፋሲሊቲ( የሙከራ ጣቢያ፣ ላቦራቶሪ፣ ተሸከርካሪ)፣ የተልዕኮ አፈጻጸም(ቴክኖሎጅ ማላመድና ማፍለቅ የተሠሩ ሥራዎችንና የወጡ ቴክኖሎጅዎችን)፣ በቅድመ ኤክስቴንሽን ሰርቶ ማሳያ የተከናወኑና በመከናወን ላይ ያሉ እንዲሁም የተጠናቀቁ ሥራዎችን፣ በዘር ብዜት የተከናወኑ ስራዎችን፣ የሀብት አጠቃቀምን፣ ከአጋር አካላት ጋር ያለ ግንኙነትን፣ የሪፎርም አተገባበርን፣ የክትትልና ግምገማ ስራዎችን፣ የሪፖርትና መረጃ አያያዝ ሥራዎችን፣ በሥራ አፈፃፀም ሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን፣ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎችን እና 2012 በጀት ዓመት ዕቅዳቸውን በማብራራት አቅርበዋል፡፡

በመቀጠልም የኢንስቲትዩቱ ቴክኒካል ዳይሬክቶሬቶች በሰብል፣ በእንስሳት፣ በአፈርና ውሃ፣ በማህበራዊ ምጣኔ ሃብትና ግብርና ኤክስቴንሽን፣ በደን፣ በቴክኖሎጅ ብዜትና ዘር ምርምር የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራት ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች በሁሉም ሪፖርት አቅራቢዎች( የምርምር ማዕከላት ዳይሬክተሮችና የኢንስቲትዩቱ ቴክኒካል ዳይሬክተሮች) መልስ እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር / ጥላዬ ተክለወልድ እና የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤርሚያስ አባተ በተነሱት እና ባልተዳሰሱት ጥያቄዎች ላይ ተጨማሪ ማጠናከሪያ መልስ የሰጡ ሲሆን በተለይም በምርጥ ዘር (አቅርቦት፣ ጥራት፣ ምርታማነት እና ብክነት)፣ በግብርና ሜካናይዜሽን(በእርሻ ማረሻ፣ መውቂያ እና ዘር ማበጠሪያ)፣ በእንሰሳት ጤና አጠባበቅ እና አያያዝ (ክትባት አሰጣጥ፡ የውስጥ ጥገኛ መከላከል፣ የግጦሽ እና የስነ ህይወት ደህንነት)፡ የጉልበት አጠቃቀም የሚስተዋሉ ችግሮች ላይ፣ ንብረት አያያዝንና አጠቃቅምን ድጂታላይዝ ከማድረግ አንፃር፡ የላብራቶሪዎች አጠቃቀም በተመለከተ እና በሌሎች ትኩረት በሚሹ ጉዳዩች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና የሥራ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም በኢንስቲትዩቱና በምርምር ማዕከላት የሚሰሩ ሠራተኞች ለስኬት በአንድነት እንዲረባረቡ፣ የሥራ ዲስፕሊንን በማክበርና መመሪያን በመጠበቅ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ በማሳሰብ የኢንስቲትዩቱ አመራርም በሚነሱ ጥያቄዎች ላይ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡

በስብሰባው ላይ የኢንስቲትዩቱ የማናጅመንት ኮሚቴ አባላት የምርምር ማዕከላት ዳይሪክተሮች፣ የፋይናንስ እና የኦዲት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል::

ex

 

 

 

Last Updated ( Saturday, 07 December 2019 14:15 )
 
Print PDF
User Rating: / 4
PoorBest 

 New arriving proceedings

Andasa Participatory Agricultural Production Constraint Analysis

Adet Participatory Agricultural Production System Constraint Analysis

Debrebirhan Participatory Agricultural Production Constraint

Gondar Participatory Agricultural Production Constraints Assessment

BNJAR Vol-1 No-1 Final

9th and 10th Crop Proceedings

Proceedings of the 9th FRD

Proceedings of 2nd and 3rd SWIM 2018

                                                                    9th Proceeding of SEERD

                                                                  LRD 10th Proceeding Final Mesfin

Last Updated ( Saturday, 07 December 2019 14:21 )
 
Print PDF
User Rating: / 2
PoorBest 

                                በቅድመ ማስፋትና ማስተዋወቅ ስራ ማዕከላት ተሸለሙ
የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት መጋቢት 14 ቀን 2010 ዓ.ም በአካሄደው የስራ አመራር ኮሚቴ ስብሰባ በ2009/2010 ዓ.ም የመኸር ወቅት በተካሄዱ የቅድመ-ማስፋትና የማስተዋወቅ ስራዎች የተሻለ አፈፃፀም ያሳዩ ሁለት ማዕከላት እንዲሸለሙና ዕውቅና እንዲሰጣቸው ወስኗል፡፡ በዚህም ውሳኔ መሰረት የስራ አመራር ኮሚቴው ያወጣቸውን የማወዳደሪያ መስፈርቶች ማለትም
1ኛ. ስፋት ያለው የቴክኖሎጅ ቅድመ ማስፋትና ማስተዋወቅ (የቦታ ስፋት በሄ/ር፣የተካሄዱ የመስክ ቀናት ብዛት፣በመስክ ቀኑ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች ብዛት፣የተዋወቁ ቴክኖሎጅዎች ብዛት በዓይነት)፣
2ኛ. የሚዲያ ሽፋን ብዛት፣
3ኛ. ወሳኝ አካላትን (ከወረዳ እስከ አገርአቀፍ) በመስክ ቀናት ማሳተፍ፣ 
4ኛ. ከሚመለከታቸው አጋር አካላት እና የወረዳ እና የዞን ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር መስራት፣
5ኛ. ጎልቶ የወጣና ተጽዕኖ የፈጠረ ቴክኖሎጅ፣ 
6ኛ. የቴክኖሎጅው ተቀባይነትና ቀጣይነት፣
የተቋቋመው የውድድር ኮሚቴ ገምግሞ የሚለኩና የሚጨበጡ በማድረግ ውድድሩን አካሂዷል፡፡ በውድድሩም መሰረት የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል 1ኛ በመውጣት የ5 ላፕቶፕ ኮምፒዩተር መግዣ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር የተሸለመ ሲሆን የሲሪንቃ ግብርና ምርምር ማዕከል ደግሞ 2ኛ በመውጣት የ2 ላፕቶፕ ኮምፒዩተር መግዣ 40,000 (አርባ ሺህ) ብር ተሸልሟል፡፡ የሽልማቱን ዓላማ በተመለከተ ኢንስቲትዩቱ በ2010/2011 ዓ.ም የመኸር ወቅት ማዕከላቱ ስራውን የበለጠ አጠናክረው በማሰቀጠል የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ለማድረግና ሌሎች ማዕከላት የነሱን ፈለግ በመከተል የተሻለ ስራ ሰርተው ተሸላሚ እንዲሆኑ ለማነሳሳት መሆኑን በመግለጽ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

Last Updated ( Saturday, 07 December 2019 14:16 )
 
Print PDF
User Rating: / 2
PoorBest 

የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በወንበርማ ወረዳ የሚያከናውናቸው የምርምር ስራዎች የሴቶችን እኩል ተጠቃሚነት ያረጋገጠ መሆኑን ገለፀ

የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከአነስተኛ እና ጥቃቅን የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ጋር /SMIS/ በመተባበር የሚያከናውናቸው የተለያዩ የምርምር ስራዎች የሴቶችን እኩል ተጠቃሚነት ሙሉ በሙሉ ያረጋገጡ መሆኑን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት በ26/07/2010ዓ.ም የተካሄደውን የመስክ ቀን ዋቢ አድርጎ አስታወቀ፡፡

በአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል የወራሚት አትክልትና ፍራፍሬ ምርምር እና ማሰልጠኛ ንዑስ ማዕከል ዳይሬክተርና የአትክልትና ፍራፍሬ ተመራማሪ አቶ ምንውየለት ጀምበሬ እንደተናገሩት ንዑስ ማዕከሉ በ5 ወረዳዎች በወንበርማ ዚንጊኒ& በደ/አቸፈር ገልዳ& በዳንግላ ዙማ& በአየሁ ጓጉሳ ኪማራ እና በደብረ ኤልያስ ሽንብሪት ላይ በአነስተኛ መስኖ ልማት አውታሮችን በመጠቀም በአትክልት በተለይም በቲማቲም ኮቸሮ እና ሚያ እንዲሁም በሽንኩርት አዳማ ሬድ እና ቦምቤ ሬድ በተባሉ ዝርያዎች ላይ በቤተሰብ ደረጃ የተቀናጀ እና ሙሉ የአመራረት ፓኬጆችን ይዞ በመስራት ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ተመራማሪው አክለውም በምርምሩ አባወራው እና እማወራዋ ሁለቱም በእኩል አፈፃፀም ላይ እንደሚገኙ እና ሴቶች መስራት እንደሚችሉ አርዓያ የሆነ ስራ መሆኑን በመጠቆም አጠቃላይ ስራው በአርሶ አደሩ ላይ ተስፋ እና ይሁንታን ያገኘ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

አጠቃላይ ውይይቱን የመሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩ ይታፈሩ እንደተናገሩት የአነስተኛ እና ጥቃቅን መስኖ ልማት ፕሮጀክት ወንበርማ ወረዳ /ዚንጊኒ/ ጨምሮ በ8 የተለያዩ ወረዳዎች ላይ ከወራሚት ንዑስ ማዕከል ጋር በመተባበር የመስኖ ምርምርና ልማት ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልፀው ፕሮጀክቶቹ ተግባራዊ ከሆኑባቸው መካከል የአንዱን ወረዳ የ1ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን በተመለከቱበት ወቅት ወዘናቸው እና ውበታቸው እንደሚያምር ተናግረው ይህም የመስኖ ስራ ውጤት በመሆኑ ቤት ውስጥ ዓመቱን ሙሉ የሚዘገንና የሚቆርስ እህል እንዳለ አመላካች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ይህ ተግባር ብዙ ቦታ ስለማይስተዋልና አብዛኛዎቹ አርሶአደሮች የተለያየ ሰብል& አትክልትና ፍራፍሬ ከማምረት ይልቅ አንድ ዓይነት ሰብል ላይ ብቻ የሚያተኩሩ በመሆናቸው ከዚንጊኒ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ትምህርት በመውሰድ የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬ ምሳሌ ሽንኩርትንና ቲማቲምን በምግባቸው በመጨመር መመገብና ልጆቻቸውንም በመመገብ ብሩህ አዕምሮ ያለው ትውልድ ማውጣት እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም የአካባቢው ማህበረሰብ ዚንጊኒን የመሰለ ቦታ ይዞ መራብና የሰው እጅ ተመልካች መሆን እንደሌለበት ይልቅ የተለያዩ የተሻሻሉ የማንጎ& የአቮካዶና የሙዝ ዝርያዎችን በማልማት ጎጡን እንደ ይጎዲ የሙዝ መንደር የሚጎበኝ አርዓያ ቦታ ለማድረግ የልማት ስራ ቢሰራና ባለው አነስተኛ ጓሮ ደግሞ ጎመኑንና ካሮቱን ማምረት ቢችል የምግብ ዋስትናውን ከማረጋገጥ ባለፈ ተረፍረፍ ያለ ምርት ማምረት ሲቻል የገቢ ምንጭ ሊሆንና ኢኮኖሚን ሊደግፍ እንደሚችል ምክረ-ሃሳብ ለግሰዋል፡፡

በምርምሩ ተሳታፊ ሴት አርሶ አደር ቦሰና በሬ አዳማ ሬድ የተባለውን የሽንኩርት ዝርያ ከማግኘት ባሻገር በቦይ የማጠጣት ዘዴን መጠቀም ከጀመሩ ወዲህ ጉልበት እንደቆጠበላቸው እና የውሃ ብክነትን እንደቀነሰላቸው በመጠቆም በፊት ከሚጠቀሙት የማጥለቅለቅ ዘዴ በቦይ የማጠጣት ዘዴን መጠቀማቸው የሽንኩርቱ ስር በውሃ እንዳይሸረሸር@ ለጸሃይ እና ለምች እንዳይጋለጥና አፈሩም በውሃ ተጠርጎ እንዳይሄድ እንዳደረገ በመግለጽ አሰራሩ አዋጭ እና ወደፊትም ይህንኑ ዘዴ እንደሚጠቀሙ አስታውቀዋል፡፡ ሌላው አርሶ አደር መለሰ ሞላልኝ ኮቸሮ የተባለውን ቲማቲም ዝርያ መስኖን በመጠቀም የዘሩ ሲሆን የሰብሉን ቁመና ከበፊቱ አሰራርና ከሀገረሰቡ ዝርያ ጋር ሲያወዳድሩት የተሻለ አቋም እንዳለው እና በአሰራሩ ሂደትም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ አርሶአደሩ አክለውም ባህላዊው አሰራር ምን ያህል ሲጎዳቸው እንደቆየ ያሳለፉትን ጊዜ በትካዜና በፀፀት ከገለጹ በኋላ የዚንጊኒ ማህበረሰብ ስራውን በማየት በቀጣይ በዘርፉ ለመሰማራት እቅድ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም በማጠቃለያ ውይይቱ ላይ አዳዲስ ዝርያዎችና ድህረ ምርት ቴክኖሎጅዎች ስለሚቀርቡበት ከስነ-አመጋገብ ጋር ተያይዞ በወረዳው ያለውን ጎላ ያለ ችግር መፍታት የሚያስችል የምርምር ውጤት ስለሚመከርበት ፍራፍሬ ላይ ሙከራ ስለሚካሄድበት ዘላቂ ድጋፍና ክትትል ስለሚደረግበት እና ቀጣይ በሚካሄዱ ሰርቶ ማሳያ እና የቅድመ ማስፋት ስራዎች እንዲሁም የመስክ ቀናት ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሰፊ የሃሳብ ልውውጥ ከተደረገና የመፍትሄ ሃሳብ ከተጠቆመ በኋላ የዕለቱ የመስክ ቀን ተጠናቅቋል፡፡    

በመስክ ምልከታው ላይ ከአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ሃላፊዎች& ተመራማሪዎችና ባለሙያዎች@ ከወራሚት ንዑስ ማዕከል ተመራማሪዎች@ ከአነስተኛ እና ጥቃቅን የመስኖ ልማት ፕሮጀክት /SMIS/ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች@ ከወንበርማ ወረዳ አስተዳዳሪዎችና የቀበሌ ግብርና ባለሙያዎች@ የአካባቢው ማህበረሰብና ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

smis

 
More Articles...
Page 9 of 34
You are here: Home